Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የፋና ላምሮት የድምጻውያን ውድድር በነገው ዕለት ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፋና ላምሮት ልዩ የባለ ተሰጥዖ ድምጻዊያን ውድድር በነገው ዕለት ይጀምራል፡፡
 
በዚህ ውድድር ለይ ተሰጥዖና ልምድ ያላቸው እና ቅድመ ማጣሪያውን ያለፉ 24 ድምፃዊያን ይሳተፉበታል፡፡
 
ውድድሩ በሙሉ የሙዚቃ ባንድ እና በቀጥታ የቴሌቪዥን ሥርጭት የሚተላለፍ ሲሆን ዳኝነቱም በሦስት ታዋቂ የሙዚቃ ሞያተኞች እና በተመልካች በሚሰጥ የኤስ ኤም ኤስ የድምፅ ውጤት ይዳኛል፡፡
 
ለስድስት ሳምንታት ብቻ ለሚካሄደው ውድድር 250ሺህ ብር ሽልማትም ተዘጋጅቷል፡፡
ፕሮግራሙ ዘውትር ቅዳሜ ከ 7፡00-10፡00 ሰዓት በፋና ቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል፡፡
Exit mobile version