Fana: At a Speed of Life!

ልማት ባንክ በተጠናቀቀው በጀት አመት 11 ቢሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ከሰጠው ብድር ሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በተጠናቀቀው 2014 በጀት አመት 10 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ከሰጠው ብድር መሰብሰብ መቻሉን ገለፀ።

ባንኩ የትግራይ ክልል ፕሮጀክቶችን ሳይጨምር የተበላሸ ብድር ደረጃን ወደ 17 በመቶ ማውረድ መቻሉንም አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዮሃንስ አያሌው እንዳስታወቁት ÷በትግራይ ያሉ በርካታ ፕሮጀክቶች ወደ ተበላሸ ብድር መግባታቸው አመቱን ለባንኩ ፈታኝ አድርጎታል።

የገጠመውን ችግር ለማካካስ ፈጣን ለውጦችን ማድረግ በመቻሉ ትግራይን ሳይጨምር በ2013 ዓ.ም የነበረውን የተበላሸ የብድር ደረጃ ከነበረበት 15 ቢሊየን ብር በበጀት አመቱ ወደ 9 ቢሊየን ብር ዝቅ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።

ባንኩ 11 ቢሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ከብድር መሰብሰቡን ጠቅሰው በበጀት ዓመቱ 3 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ማትረፍ መቻሉን ገልፀዋል።

በብድር አሰባሰብ ላይ የጀመረውን ስራ በማጠናከር በተያዘው 2015 በጀት አመት 14 ቢሊየን ብር ከብድር ለመሰብሰብ ማቀዱንም አስረድተዋል።

የተበላሸ ብድር ደረጃን በ2014 በጀት አመት ከነበረበት 17 በመቶ በተያዘው በጀት አመት ወደ 10 በመቶ ለማውረድ እንደታቀደ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.