ዓለምአቀፋዊ ዜና

ኬንያውያን ቀጣይ ፕሬዚዳንታቸውን እየመረጡ ነው

By Mekoya Hailemariam

August 09, 2022

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዛሬ በመካሄድ ላይ ይግኛል።

ተሰናባቹን ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታን ለመተካት እየተካሄደ ባለው ምርጫ አራት እጩዎች ቀርበዋል።

ሆኖም በምርጫው፥ የአሁኑ የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ እና የሀገሪቱ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ዋነኛ ተፎካካሪዎች ናቸው።

ለምርጫው 22 ሚሊየን ኬንያውያን የተመዘገቡ ሲሆን፥ 40 ሺህ የምርጫ ጣቢያዎችም ተቋቁመዋል።

ከፕሬዚዳንታዊ ምርጫው በተጨማሪም ዜጎች የፓርላማ አባላትን እና ሴናተሮችንም በመምረጥ ላይ ይገኛሉ።

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ