Fana: At a Speed of Life!

በአቡ ዳቢ በሙቀት መጨነቅ የ4 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 03፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ሁለት ወራት በተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ከፍተኛ የሙቀት መጨመርና በሰውነት ሙቀት መጨናነቅ ምክንያት በትንሹ የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ገልፍ ኒውስ ዘግቧል።
ከአራቱ ተጎጂዎች መካከል ሦስቱ በረሃ ውስጥ መንገዳቸውን የሳቱ እና በጊዜው የሕክምና እርዳታ ያላገኙ ሲሆኑ፤ አራተኛው ተጎጂ ደግሞ የጉልበት ሰራተኛ ነው ሲል የአቡ ዳቢ ፖሊስ ገልጿል።
በሙቀት መጨናነቅ ችግር ሰውነት ሙቀትን መቆጣጠር በማይችልበት ጊዜ የሚከሰት የጤና እክል እንደሆነ ባለሙያዎች ያብራራሉ፡፡
የሁኔታው የመጀመሪያ ደረጃ ችግር ከመጠን በላይ የውሃ እና የጨው መጠን ከሰውነት መጥፋት ስለሚያስከትል ችግሩ የሕክምና ክትትል በሌለበት እንደሚባበስ የተገለጸ ሲሆን፥ ለከፍተኛ ሙቀት መጋለጡ ከቀጠለ ቀስ በሙቀት መጨመሩ ይባባስና ለሞት ሊዳርግ እንደሚችል ነው የተመላከተው፡፡
የ50 ዓመቱ የኢሚሬትስ ጡረተኛ እና በግብርና የሚተዳደሩት ግለሰብ፥ መንገድ ጠፍቶባቸው በረሃ ውስጥ በሙቀት ሕይወታቸው አልፎ መገኘቱን አንድ የፖሊስ ባለሥልጣን ተናግረዋል።
ሌሎቹ ሕይወታቸው ያለፈው የ26 እና የ30 ዓመት ሰዎች የፓኪስታን ዜጎች እንደሆኑና በከብት እረኝነት የተሰማሩ እንደነበር አብራርተዋል። ሁለቱም በረሃ ውስጥ በመጓዝ ላይ ሳሉ ሕይወታቸው እንዳለፈ ነው ባለስልጣኑ አክለው የገለፁት፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.