Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ለትርፍ ያልተቋቋመውን የአይሁዶች ድርጅት እንዳታግድ የእስራኤል ፕሬዚዳንት ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 03፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ ለትርፍ ያልተቋቋመ የአይውድ ድርጅትን ሥራ ለማገድ እየተደረገች ያለውን ግፊት እንድታቆም ለማግባባት የእስራኤሉ ፕሬዚዳንት ከሩሲያው አቻቸው ጋር በስልክ ተወያዩ፡፡

የእስራኤል ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ ከሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር ዛሬ ባደረጉት ውይይት፥ ሩሲያ በዓለም ላይ ትልቁን የአይሁዶች ለትርፍ ያልተቋቋመ ተቋም ለማገድ እያደረገች ስላለው ሁኔታ አንስተው መክረዋል።

ወደ 600 ሺ የሚጠጉ ሩሲያውያን በአይሁዶች በብዛት ወደ እስራኤል የሚጓዙ ሲሆን፣ አለመግባባቱ ከተከሰተ ጀምሮ የአመልካቾች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱንም ባለስልጣናት ተናግረዋል።

የሩስያ የፍትህ ሚኒስቴር ሕግ ጥሷል በሚል በሩስያ የአይሁድ ኤጀንሲ ቅርንጫፍን በመወንጀል እንደሚፈልገውና እንቅስቃሴውም ሊታገድ እንደሚችል ነው የተገለፀው።

አንዳንድ የእስራኤል ፖለቲከኞች ሩሲያ በዩክሬን ላይ ባካሄደችው ወታደራዊ ዘመቻ ከእስራኤል ለተሰነዘረባት ትችት በምትወስደው የበቀል እርምጃ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመው፥ የሩስያ የአይሁድ ማህበረሰብ ላይ ጫና ሊያሳድር ይችላል ሲሉም ስጋታቸውን ገልጸዋል።

አንዳንዶች ደግሞ ሞስኮ የሶሪያን መንግሥት ለመደገፍ የአየር ኃይል ባሰማራችበት እና እስራኤል “በኢራን የሚደገፉ ታጣቂዎች” ባለቻቸው አካላት ላይ ከምታደርሰው የማጥቃት እንቅስቃሴ ጋር በማያያዝ የሩሲያ -እስራኤል ግንኙነትን ሊጎዳ ይችላል ብለው ይሰጋሉ።

ይሁንና ፕሬዚዳንት ሄርዞግ የስልክ ውይይቱ ግልጽ እንደነበር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የገለጹ ሲሆን፥ በሀገራቱ መካከል ባሉት አስፈላጊ የትብብር መስኮች ግንኙነታቸውን ለመቀጠል መስማማታቸውን ተናግረዋል፡፡

የክሬምሊን መንግሥት በበኩሉ፥ የአይሁድ ኤጀንሲን በተመለከተ ግንኙነቶች በሁለቱም ሀገራት በኩል እንደሚቀጥሉ ከስምምነት መደረሱን ገልጿል።

ምንጭ፡- ሲጂቲኤን እና አሸርቅ አል አውሰጥ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.