Fana: At a Speed of Life!

አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት በኢኮኖሚው ዘርፍ የድርሻቸውን እንዲወጡ ምቹ ሁኔታ ይመቻቻል-ብሄራዊ ባንክ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት በኢኮኖሚው ዘርፍ የድርሻቸውን እንዲወጡ የማስቻል ስራ ላይ ትኩረት አድረጎ እንደሚሰራ ብሄራዊ ባንክ ገለጸ፡፡
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት በብሄራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማት ሱፐር ቪዥን ምክትል ገዢ ሰለሞን ደስታ÷አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት በምጣኔ ሃብቱ መስክ ያላቸው ሚና ከፍ እንዲል እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡
 

2 ሺህ 80 እውቅና ኖሯቸው እየተንቀሳቀሱ ያሉ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት ጠቅላላ ካፒታላቸው 11 ቢሊየን ብር በላይ መድረሱንም አቶ ሰለሞን ተናግረዋል፡፡

 
ተቋማቱ ጤናማ የሚባል እንቅስቃሴ እንዳላቸው የጠቀሱት አቶ ሰለሞን÷በቴክኖሎጂው ዘርፍ ያለውን ክፍተት እንዲሞሉ ድጋፍና ክትተል እየተደረገ ነው ብለዋል ፡፡
 
ለተቋማቱ የብድር አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ጥናት እየተደረገ እንደሆነም አንስተዋል፡፡
 
የሸገር ብድር እና ቁጠባ ተቋም ስራ አስኪያጅ አቶ አማኑኤል ጸጋዬ በበኩላቸዉ÷መሰል ተቋማት አቅማቸውን ያሳድጉ ዘንድ መንግስት ድጋፉን ሊያጠናክር ይገባል ብለዋል ፡፡
 
በአወል አበራ
 
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.