10 ሚሊየን ብር በደረቅ ቼክ ያጭበረበረችው 10 ዓመት ተፈረደባት
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቂ ስንቅ ሳይኖራት ቼክ በማውጣት ወንጀል የተከሰሰች ግለሰብ በ10 ዓመት ፅኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጣች፡፡
ተከሳሽ ፍጥረት አማረ ያዘው በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ ማውጣት ወንጀል ለመደንገግ የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 693/1 የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፏ ክስ ተመስርቶባታል፡፡
ተከሳሽ በቂ ስንቅ (በቂ ገንዘብ) ሳይኖራት ለገዛችው የቤት ዕቃ ክፍያ ለመፈፀም 10 ሚሊየን ብር እንዲሁም በብድር መልክ ለወሰደችው ገንዘብ ክፍያ 600 ሺህ ብር ደረቅ ቼክ ፈርማ መስጠቷን የፍትሕ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
ተከሳሽ የእምነት ክህደት ቃሏን ስትጠየቅ ”እኔ ድርጊቱን አልፈፀምኩም ጥፋተኛም አይደለሁም ”ስትል ቃሏን ሰጥታለች።
ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ የምስክሮች ቃል እና የሰነድ ማስረጃዎችን በበቂ ሁኔታ ለችሎቱ በማስረዳቱ÷ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ የወንጀል ችሎት በተከሳሽ ላይ በሁለቱም ክሶች የጥፋተኝነት ፍርድ ሰጥቷል።
በዚህም ተከሳሽን ያርማል መሰል አጥፊዎችንም ያስተምራል በማለት ተከሳሽ በ10 ዓመት ፅኑ እስራትና 50 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንድትቀጣ ተወስኖባታል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!