የሀገር ውስጥ ዜና

በጋምቤላ የፀጥታ ችግሮችን ለመፍታት ውይይት እየተካሄደ ነው

By Feven Bishaw

August 10, 2022

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል የፀጥታ ምክር ቤት በክልሉ የሚስተዋሉ የፀጥታና የሰላም ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት በሚያስችል ሁኔታ ላይ ውይይት እያካሄደ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ÷ በክልሉ የፀጥታ ምክር ቤት አደረጃጀት እና የበታች የፀጥታ ምክር ቤቶችን በሚገባ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት እየተካሄደ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡