Fana: At a Speed of Life!

የ165 ነጥብ 2 ሚሊየን ዶላር የእርዳታና የብድር ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመሬት መራቆትን በመቀንስ ምርታማነትን ለመጨመር የሚውል የ165 ነጥብ 2 ሚሊየን ዶላር የእርዳታና የብድር ስምምነት ተፈረመ፡፡

በኢትዮጵያ መንግሥትና በዓለም ባንክ መካከል መካከል የተደረገው ስምምነት በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ 170 ወረዳዎችና በ217 ተፋሰሶች ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን÷ የተፈጥሮ ሀብት ልምዶችን  በማስፋፋት በ789ሺህ ቤተሰቦች ውስጥ የታቀፉ 4 ሚሊየን ወገኖችን ተጠቃሚ ያደረጋል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም በተደረገው ድጋፍ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ለድርቅ ተጋላጭ የሆኑና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን አርሶ አደሮችን ኑሮ ለማሻሻል የሚውል መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በግሪን ክላይሜት ፈንድ (GCF) ከተገኘውና በአለም ባንክ በኩል ተግባራዊ ከተደረገው በጀት ውስጥ 58 ሚሊየን ዶላሩ በዕርዳታ መልኩ የተሰጠ ሲሆን÷ 107 ሚሊየን ዶላሩ ደግሞ በረጅም ጊዜ የሚከፈል  ብድር መሆኑ ታውቋል፡፡

የገንዘብ ድጋፍ ስምምነቱን በገንዘብ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ትብብር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው እና በአለም ባንክን  የግሪን ክላይሜት ፈንድ ተወካይ አቶ አሳዬ ለገሰ መፈረሙን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.