Fana: At a Speed of Life!

በብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል አከባበር ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች በ17ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል መሪ ዕቅድ ላይ ተወያይተዋል፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር÷ውይይቱ ባለፉት ዓመታት በበዓሉ አፈጻጸም የተስተዋሉ ክፍተቶችን በመሙላት እና የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን በመቀመር የተሻለ ዕቅድ አዘጋጅቶ ወደ ሥራ የሚያስገባ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በውይይት መድረኩ የ17ኛው በዓል አከባበር መሪ ዕቅድ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓላት ላይ የተካሄደ የዳሰሳ ጥናት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
ተሳታፊዎች ቀጣዩ በዓል የሕዝቦችን ዴሞክራሲያዊ አንድነት የበለጠ እንዲያጠናክርና ውጤታማ በዓል እንዲሆን አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ ማንሳታቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በዚህም ከሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት፣ ዴሞክራሲያዊ አንድነትን ከማጎልበት፣ ከልማት፣ ከሰላም፣ ከበጎ አድራጎት፣ ከባህል ልውውጥ፣ ከፈጠራ ሥራዎች እንዲሁም ከቱሪስት መስህብነት አንጻር የተቃኙ ሥራዎችን ብሎም በዳሰሳ ጥናቱ የተገኙ ውጤቶችን በዕቅዱ አካቶ ወደ ሥራ መግባት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡
17ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሐዋሳ ከተማ እንደሚከበር ይታወቃል፡፡
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.