Fana: At a Speed of Life!

ዋልያወቹ በቻን ማጣሪያ የመጨረሻ የደርሶ መልስ ጨዋታ የሚያደርጉበት ቀንና ቦታ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሩዋንዳ ብሔራዊ ቡድን ጋር በቻን ማጣሪያ የመጨረሻ የደርሶ መልስ ጨዋታውን የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎቹን የሚያደርግበት ቀናት እና ቦታ ይፋ ሆኗል፡፡

በመጀመሪያው ጨዋታ ኢትዮጵያ ባለሜዳ የምትሆን ሲሆን÷ በዚህም ነሐሴ 20 ቀን 2014 ዓ.ም በታንዛንያ ዳሬሰላም ቤንጃሚን ምካፓ ስታዲየም ላይ ጨዋታዋን የምታደርግ ይሆናል።

እንዲሁም የመልሱን ጨዋታ ነሐሴ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ሩዋንዳ ላይ የሚደረግ ይሆናል፡፡

ትናንት የተሰባሰበው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለጨዋታዎቹ በአዳማ ዝግጅት ሲያደርግ ከቆየ በኋላ ነሐሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም ወደ ታንዛንያ እንደሚያቀና የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.