የሀገር ውስጥ ዜና

ምክር ቤቱ በሁሉም ዘርፎች የሚደረገው ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቀረበ

By Meseret Awoke

August 11, 2022

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሁሉም ዘርፎች የሚደረገው ትብብር እና አንድነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቀረበ፡፡

ምክር ቤቱ ፥ ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ 2ኛ ተርባይን ዛሬ ኃይል ማመንጨት መጀመሩን አስመልክቶ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

በመልዕክቱም ÷ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የሁሉም ኢትዮጵያውያን አሻራ ያረፈበት ፤ ከፍተኛ የገንዘብና ዘርፈ ብዙ መሥዋዕትነት የተከፈለበት ትልቅ ሀገራዊ ውጤት መሆኑን አውስቷል፡፡

ግድቡ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ያረጋገጠ ዘመን ተሻጋሪ ቅርስ ነው ሲልም አስረድቷል፡፡

ምክር ቤቱ በሁሉም ዘርፎች የሚደረገው ሀገራዊ ትብብር እና አንድነት ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርቧል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!