Fana: At a Speed of Life!

የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ 2ኛ ተርባይን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት መጀመሩን አስመልክቶ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ባስተላለፉት መልዕክት ÷የሁሉም ኢትዮጵያውያን አሻራ ያረፈበት የህዳሴው ግድባችን ሀይል ማመንጨት በመጀመሩ መላው የሀገራችን ህዝቦች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ በመልዕክታቸው ÷ይህ የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ድል የመደጋገፍና አንድነት ውጤት ነው፣ በአንድነት ከቆምን ለስኬት እንደምንበቃ ማረጋገጫ ነው ብለዋል በመልዕክታቸው፡፡

እንዲሁም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ባስተላለፉት መልዕክት ÷አንድነት ማንም የማያሸንፈው ኃይል መሆኑን ቀድመው ያወቁት ኢትዮጵያውያን ከጫፍ ጫፍ ባደረጉት ያልተቋረጠ ድጋፍ የአንድነታቸው አርማ የሆነውን ታላቁ የሕዳሴ ግድብን ወደመጨረሻ ምዕራፍ ማድረሳቸውን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ እና የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦሞድ ኡጁሉ የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ 2ኛው ተርባይን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት በመጀመሩ ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው የአንድነታችን ማሰሪያ እና የኢዮጵያዊነታችን አርማ የሆነው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሃይል ማመንጨት በመጀመሩ ሁላችሁም እንኳን አደረሳችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ባስተላለፉት መልዕክት የመጪው ብሩህ ዘመን ማብሰሪያ ሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 2ኛው ተርባይን ሃይል በማመንጨቱ እንኳን ደስ አላቹ ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ ባስተላለፉት መልክት÷ ፈተናዎቹን በፅናት አልፈን ለከፍተኛ ውጤት መድረሳችን ለጠላቶቻችን እንደማንበገር በቂ መልእክት፤ ለህዝባችን ደግሞ የፅናት ውጤት ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.