Fana: At a Speed of Life!

የሕዳሴ ግድብ የትኛውም ችግር ሳይበግረው ለስኬት መብቃቱ የህዝቡን ጥንካሬ እና ህብረት የሚያሳይ ነው – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ማንኛውም ሰው ሰራሽ ችግር ሳይበግረው ለስኬት መብቃቱ የህዝቡን ጥንካሬ እና ህብረት የሚያሳይ ነው ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ፡፡
 
ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሶስተኛ ምዕራፍ ውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁን አስመልክተው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
 
በመልዕክታቸውም፥ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ማንኛውም ሰው ሰራሽ ችግር ሳይበግረው ለስኬት መብቃቱ የህዝቡን ጥንካሬ እና ህብረት የሚያሳይ መሆኑን አንስተዋል፡፡
 
የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስኬትም የመላ ኢትዮጵያውያን አንድነት እና ትብብር ውጤት ነው ብለዋል፡፡
 
ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነት ላይ ያጋጠሟትን ፈተናዎች ተስፋ እንዳልቆረጠች እና ወደፊትም አመርቂ ድሎችን እንደምታስመዘግብ ተናግረዋል።
 
አቶ ሽመልስ ኢትዮጵያውያን በህዳሴ ግድብ ግንባታ ያሳዩትን አንድነት በሌሎች የልማት ስራዎች ላይ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ማቅረባቸውንም ከርዕሰ መስተዳድሩ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.