Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ብርቱካን ከተመድ የምስራቅ አፍሪካ የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከምስራቅ አፍሪካ የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ዳኒኤል ኤንድሪስ ጋር ተወያይተዋል፡፡
 
በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እየተደረጉ ያሉ የሰብዓዊ ድጋፎችን አጠናክሮ መቀጠል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
 
አምባሳደር ብርቱካን በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች ያልተቋረጠ የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደርስ መንግስት እያከናወነ ያለውን በጎ ስራ እና እያሳየ ያለውን ቁርጠኝነት አስረድተዋል፡፡
 
የሰብዓዊ እርዳታው ተጠናክሮ እንዲቀጥልም የሰብዓዊ ድርጅቶች እና ለጋሽ አካላት ብርቱ ትብብር ማድረግ እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡
 
ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚሰጡ አገልግሎቶች ሁሉ ምቹ እና ቀልጣፋ እንደሚሆኑ ሚኒስትር ዴኤታዋ አረጋግጠዋል።
 
በተመድ የምሥራቅ አፍሪካ የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ዳኒኤል ኤንድሪስ በበኩላቸው÷ ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች ተከታታይ እና ጠንካራ የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደርስ መንግስት እያሳያ ያለውን ቁርጠኝነት አድንቀዋል፡፡
 
በቀጣይም ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የሚደረገው ሰብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
ሁለቱ አካላት በቀጣይ ድጋፍ ሰጪ አካላቶችን በማስተባበር የተጠናከረ የሰብዓዊ ድጋፎች ተደራሽ እንዲሆኑ በትብብር ለመስራት መምከራቸው ተገልጿል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.