የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ 1 ሺህ 132 ተማሪዎችን አስመረቀ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 1 ሺህ 132 ተማሪዎችን አስመርቋል።
በ2004 የተቋቋመው አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ያስመረቀው ለዘጠነኛ ዙር ነው።
ተማሪዎቹ በመደበኛ፣ በማታ፣ በክረምት፣ በድህረ ምረቃ እና ቅድመ ምረቃ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸውም ነው የተባለው፡፡
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ የዩንቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ከማል አብዱራሂምን ጨምሮ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ አምባሳደሮች፣ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ከማል አብዱራሂም በመርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ ዩኒቨርሲቲው በግብርና፣ በሀገር በቀል እውቀትና በጤና ዘርፍ በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-