Fana: At a Speed of Life!

አዋሽ ውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት የሜካናይዝድ ሙያተኞችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዋሽ ውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት በተለያዩ ሙያዎች ያሰለጠናቸውን የሜካናይዝድ ሙያተኞች አስመረቀ፡፡

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ የተገኙት የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጀኔራል ይመር መኮንን÷ የአዋሽ ውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት የሰራዊቱን የሜካናይዝድ ክፍሎች በትምህርትና ስልጠናዎች ብቁ ሙያተኞችን ማፍራት ዋናው ተልዕኮ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አሸባሪው የህወሓት ቡድን ኢትዮጵያን በተዳፈረበት ወቅት ዘርፈ ብዙ ተልዕኮዎችን በመፈፀም ሀገር የማዳን ኃላፊነቱን በብቃት ተወጥቷልም ነው ያሉት፡፡

በቀጣይም መከላከያ የሜካናይዝድ ክፍሎች ላይ በትኩረት ለመስራት ቁርጠኛ ነው ብለዋል፡፡

ተመራቂ የሜካናይዝድ ሙያተኞች በቆይታቸው የሀገር ሉዓላዊነትን መጠበቅ የሚያስችሉ ስልጠናዎችን መወሰዳቸውን የገለጹት ደግሞ የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ባላው ምንተስኖት ናቸው፡፡

አካባቢው የኢትዮጵያ ወጪና ገቢ ማስተናገጃ ጎዳና በመሆኑ በአካባቢው የአሸባሪው ሸኔን እንቅስቃሴ ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን መግታት መቻሉን ተናግረዋል፡፡

ተመራቂ የሜካናይዝድ ሙያተኞች በበኩላቸው፥ በስልጠና ቆይታቸው የተሻለ ሙያዊ አቅም መፍጠራቸውን ጠቁመው፥  በቀጣይ የሚሰጣቸውን ሀገራዊ ተልዕኮ በብቃት መወጣት እንደሚችሉ አረጋግጠዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.