Fana: At a Speed of Life!

የሩሲያ-ቻይና የንግድ ልውውጥ ትልቅ ምዕራፍ ላይ መድረሱ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሩሲያ እና በቻይና መካከል ያለው ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት የማያቋርጥ እድገት እያሳየ መምጣቱ ተነግሯል፡፡

የሀገራቱ የንግድ ግንኙነት ጠንካራ እድገትን እያሳየ ያለው አስቸጋሪ ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች ባሉበት ነው ተብሏል።

በዚህ አመት የንግድ ልውውጡ 200 ቢሊየን ዶላር ሊደርስ እንደሚችል በሩሲያ የቻይና አምባሳደር ያላቸውን ግምት በትናንትናው ዕለት አስቀምጠዋል፡፡

“የሩሲያ-ቻይና ንግድ እና ኢኮኖሚያዊ ትብብር ከወረርሽኙ ጋር የተዛመዱ ፈተናዎች፣ የአለም ኢኮኖሚ መዋዠቅ እና አስቸጋሪ ዓለም አቀፍ እና ቀጠናዊ ሁኔታዎች ቢኖሩም ጥሩ ውጤቶችን እና ዘላቂ እድገትን እያሳየ ይገኛል” ሲሉ አምባሳደር ዣንግ ሃንሁይ ለሪያ ኖቮስቲ የዜና ወኪል ተናግረዋል።

በዓመቱ የመጀመሪያዎቹ ሰባት ወራት የቤጂንግ-ሞስኮ የንግድ ልውውጥ በ29 በመቶ በማደግ 97 ነጥብ 71 ቢሊየን ዶላር መድረሱን አምባሳደሩ የቻይና የጉምሩክ መረጃን በመጥቀስ አስታውቀዋል።

በዚህ ጊዜ ውስጥ ቻይና ወደ ሩሲያ 36 ነጥብ 26 ቢሊየን ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን የላከች ሲሆን፥ አጠቃላይ የ5 ነጥብ 2 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ብለዋል፡፡

ከ2021 ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም ከሩሲያ የገባው ሸቀጥ በ48 ነጥብ 8 በመቶ ከፍ ያለ ሲሆን፥ ይህም ወደ 61 ነጥብ 44 ቢሊየን ዶላር ደርሷል ብለዋል፡፡

የሁለትዮሽ ንግዱ  ቅድሚያ የሚሰጣቸውን አንዳንድ ጉዳዮች በመዘርዘር ዣንግ የሀይል አቅርቦትን፣ ኒውክሌር ሃይልን፣ አቪዬሽን፣ ህዋ፣  መሠረተ ልማትን እንዲሁም ዲጂታል ቴክኖሎጂን፣ መድኃኒትን፣ አረንጓዴ ኢነርጂን፣ ግብርናን፣ ሳይንስ እና ፈጠራ የጎላ ድርሻ እንደሚይዙ ተናግረዋል፡፡

“እነኚህ ሁሉ የንግድ እና የኢኮኖሚ ትብብራችን ወደ አዲስ ምዕራፍ ለመድረስ ጠንካራ መሰረት ይጥላሉም” ብለዋል፡፡

ምንጭ፦  አርቲ

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.