Fana: At a Speed of Life!

ለአትሌቲክስ ልዑካን ቡድኑ የሽልማትና እውቅና መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን የሽልማትና እውቅና መርሐ ግብር በስካይላይት ሆቴል ተካሄደ፡፡
 
በሽልማትና እውቅና መርሐ ግብር ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር፣የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ እና የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ ሌሎች የፌዴሬሽኑ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
 
በመርሐ ግብሩ ለቡድን መሪዎች ከ40 ሺህ ብር እስከ 75 ሺህ ብር ሽልማት የተበረከተ ሲሆን÷የወርቅ ሜዳሊያ ላመጡ አትሌቶች የ300 ሺህ ብር፣ የብር ሜዳሊያ ላመጡ ደግሞ የ200 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቷል፡፡
 
በተጨማሪም የነሐስ ሜደሊያ ላመጡ የ100 ሺህ ብር እንዲሁም ዲፕሎማ ላገኙት አትሌቶች የ50 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
 
በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወርቅ ሜዳሊያ ላመጡ አትሌቶች የ 150 ሺህ ብር፣ የብር ሜዳሊያ ላመጡ የ100 ሺህ ብር እንዲሁም የነሐስ ሜደሊያ ላመጡ አትሌቶች የ 75 ሺህ ብር ሽልማት አበርክቷል፡፡
 
በተመሳሳይ የወርቅ ሜዳሊያ ላስገኙ አሰልጣኞች የ300 ሺህ ብር፣ የብር ሜዳሊያ ላስገኙ የ200 ሺህ ብር፣ የነሃስ ሜዳሊያ ላስገኙ የ100 ሺህ ብር እንዲሁም ዲፕሎማ ላስገኙ የ50 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
 
በኮሎምቢያ ካሊ በተካሄደው 19ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.