አረንጓዴ አሻራ የጠፉ የተፈጥሮ ሀብቶቻችንን የመለሰ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የጠፉ የተፈጥሮ ሀብቶቻችንን የመለሰ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሐረር ከተማ አረንጓዴ አሻራቸውን በዛሬው ዕለት አኑረዋል ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት እንደገለጹት፥ ባለፉት አራት ዓመታት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ለኢትዮጵያ አዋጭ መሆኑ በብዙ ማሳያዎች ተረጋግጧል።
አረንጓዴ አሻራ የጠፋ የተፈጥሮ ሀብቶችን እንደሚመልስ ሐረማያ ሐይቅን በማንሳት ከሐረሪ ህዝብ በላይ ምስክር የለም ብለዋል።
በአልዓዛር ታደለ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!