Fana: At a Speed of Life!

አቡበከር ናሰር ለማሜሎዲ ሰንዳውንስ የመጀመሪያ ግቡን አስቆጠረ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊው አቡበከር ናሰር ለደቡብ አፍሪካው ክለብ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ የመጀመሪያ ግቡን አስቆጥሯል፡፡
 
በአሬና ስታዲየም በተደረገው የሰንዳውንስ እና የካይዘር ቺፍስ ጨዋታ አቡበከር በ76ኛው ደቂቃ ላይ ተቀይሮ በመግባት ነው ለክለቡ 4ኛውን ለራሱ ደግሞ የመጀመሪያውን ግብ ማስቆጠር የቻለው፡፡
 
በዕለቱ በተደረገው ጨዋታ የግብ አካውንቱን የከፈተው አቡበከር ድንቅ ብቃቱን ማሳየት የቻለ ሲሆን÷ በጨዋታው ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ካይዘር ቺፍስ 4 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል፡፡
 
የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና እና የዋሊያዎቹ አጥቂ አቡበከር ናስር በደቡብ አፍሪካ ከሳምንት በፊት የማሜሎዲ ሰንዳውንስ ዝውውሩን አጠናቆ የፊፋ አይ ቲ ሲ ማረጋገጫ ማግኘቱ የሚታወስ ነው፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.