Fana: At a Speed of Life!

በ336 ሚሊየን ብር የተገነባ የገበያ ኢንተርፕራይዝ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህር ዳር ከተማ በ336 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የግብርናና የተቀነባበሩ የግብርና ምርቶች መዳረሻ ገበያ ኢንተርፕራይዝ ዛሬ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
 
የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር የህዝብ ግንኙነት አማካሪ አቶ ሞላ መልካሙ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ እንዳሉት÷የኢንተርፕራይዙ መቋቋም የግብርና ምርቶችን ለተጠቃሚው ህብረተሰብ ህግና ሥርዓትን ተከትሎ ለማቅረብ ያግዛል።
 
በክልሉ የሚመረተው ምርት ለሸማቹ ህብረተሰብ ፍትሃዊነቱን ጠብቆ እየደረሰ አለመሆኑን የገለፁት አማካሪው÷ ኢንተርፕራይዙ ችግሩን ለመፍታት የጎላ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።
 
የኢንተርፕራይዙ አመራሮችና ሰራተኞችም በቀጣይ አምራችና ሸማቹን ባጠረ ግብይት በማስተሳሰር ስኬታማ ስራዎችን መስራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።
 
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ ባለሃብቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.