Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል ኩታ ገጠም እርሻ ያስገኘው ምርት የሚያስደንቅ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ኩታ ገጠም እርሻ ያስገኘው ምርት የሚያስደንቅ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሶማሌ ክልል ፋፈን ዞን በዘመናዊ መንገድ እየለማ ያለን የስንዴ እርሻ ጎብኝተዋል፡፡

ኩታ ገጠም እርሻው ከ8 ሚልየን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚያስገኝ ይጠበቃል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ።

ይህም÷ ቀደም ሲል ተዘንግተው የቆዩ ስፍራዎች ወደ ምርታማነት የመለወጣቸው ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

“እነዚህ ጥረቶች ሊጠናከሩና ሊስፋፉ ያስፈልጋል፣ አስተሳሰባችን እና ተግባሮቻችን ሙሉ በሙሉ በምርታማነት እና ልማት ላይ ማተኮር አለባቸው” ሲሉም አሳስበዋል።

በክልሉ በዚህ ወቅት 127 ሺህ 277 ሄክታር መሬት በስንዴ ምርት መሸፈኑ ተገልጿል።

በተያዘው በጀት አመትም በክልሉ ከ847 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዋና ዋና ሰብሎች እንደሚሸፈን በጉብኝቱ ተገልጿል ።

ሰብልና ክብካቤ በሶማሊኛ “ደለግ እና ደሪዬል” በሚል ፕሮግራም ክልሉ ያለውን እምቅ የተፈጥሮ አቅም በመጠቀም ህዝቡን ከድህነት ለማውጣት ይሰራልም ተብሏል፡፡

በአላዛር ታደለ

ተጨማሪ መረጃ÷ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ማህበራዊ ትስስር ገጽ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.