Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ማክሮን ፊንላንድ እና ስዊድን ኔቶን እንዲቀላቀሉ ፈቀዱ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፊንላንድ እና ስዊድን ኔቶን ለመቀላቀል ያቀረቡት ጥያቄ ከ20 በላይ በሚሆኑ የኔቶ አባል ሀገራት ይሁንታ ማግኘቱ ተገለጸ።

ባሳለፍነው ማክሰኞ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለሁለቱ የኖርዲክ ሀገራት ይሁንታን የሚቸር ፊርማ መፈረማቸው ይታወሳል።

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮንም ለሀገራቱ ይሁንታቸውን በፊርማቸው እንዳረጋገጡላቸው ተሰምቷል፡፡

ባሳለፍነው ግንቦት ወር ቱርክ በአሸባሪነት ለፈረጀቻቸው ኩርዶች ስዊድን እና ፊንላንድ ድጋፍ ያደርጋሉ በሚል የሀገራቱን የአባልነት ጥያቄን ውድቅ እንደምታደርግ መዛቷ ይታወሳል።

አሁን ላይ በቱርክ እና በሀገራቱ መካከል የነበረው ጊዜያዊ አለመግባባት ወደ ሥምምነት ያመራ ይመስላልም ተብሏል፡፡

ስዊድንም ባሳለፍነው ሐሙስ አንድ ቱርክ የምትፈልገውን ዜጋ አሳልፋ ለመስጠት ቃል ገብታለች፡፡

የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ ÷ በፈረንጆቹ በዚህ ወር መጨረሻ ላይ የፊንላንድን እና የስዊድንን ባለሥልጣናት አግኝተው ኔቶን ለመቀላቀል ባስገቡት ማመልከቻ ላይ እንደሚወያዩ መናገራቸውን አር ቲ ዘግቧል።

ፊንላንድ እና ስዊድን ያቀረቡት ኅብረቱን የመቀላቀል ጥያቄ እንዲጸድቅ በሠላሳዎቹ የኔቶ አባል ሀገራት ተቀባይነት ማግኘት አለበት፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.