ዓለምአቀፋዊ ዜና

በግብጽ በእሳት አደጋ የ41 ሠዎች ህይወት አለፈ

By ዮሐንስ ደርበው

August 14, 2022

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 8 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በግብጽ በቤተክርስቲያን ውስጥ በተነሳ የእሳት አደጋ የ41 ሠዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ።

በቤተክርስቲያኑ ውስጥ 5 ሺህ ምዕመናን የሰንበት ቅዳሴ እያስቀደሱ እንደነበር የቢቢሲ ዘገባ ያመላክታል።

በጊዛ በሚገኘው አቡ ሰፊን ቤተክርስቲያን እሳት አደጋ ለህልፈት ከተዳረጉት በተጨማሪ በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውም ነው የተሰማው።

የአደጋው መንስኤ ከኤሌክትሪክ ጋር የተያያዘ ሳይሆን እንደማይቀር ፖሊስ አስታውቋል።