Fana: At a Speed of Life!

አስተማማኝ ወታደራዊ ኃይል ለመገንባት እየተሰራ ነው – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 በጀት ዓመት ለሰራዊቱ የተሟላ ሎጂስቲስቲክስ በማቅረብ አስተማማኝ ወታደራዊ ኃይል ለመገንባት እየሰራን ነው ሲሉ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ።

የመከላከያ ሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ ከሁሉም ዕዞች ከተውጣጡ የሎጂስቲክስ አመራሮች ጋር ዓመታዊ የሥራ አፈፃፀምን በመገምገም ለጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለፃ አቅርበዋል።

በዚሁ ወቅት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ÷ “ጠላቶቻችን ግንባር ፈጥረው ቢሰለፉም ለሰራዊታችን የተቀናጀ ሎጂስቲካዊ ፍላጎቶችን በማቅረብ ከሰራዊቱ ጀግንነት ጋር ተዳምሮ ጠላትን ማሳፈር ችለናል “ብለዋል።

በ2015 በጀት ዓመት ሰራዊቱ ዘመኑ ያፈራቸውን ወታደራዊ ቴክኖሎጂዎች እንደሚታጠቅ ጠቅሰዋል፡፡

የሎጂስቲክስ አሰራር እና ስርዓት በሚፈቅደው ልክ ሰራዊቱ በሚያስፈልገው ቦታ እና ሰዓት የሚያስፈልገውን ሁሉ በማቅረብ ሎጂስቲክስ የሰራዊቱ ደጀን መሆኑን ገልጸዋል።

የመከላከያ ሎጅስቲክስ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጀኔራል አብዱራህማን እስማኤል በበኩላቸው÷ የሎጂስቲክስ ዝግጁነት ከመቸውም ጊዜ በላይ ያደገ ነው ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.