Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ከ100 ሺ ሄክታር በላይ መሬት በሩዝ እየለማ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በምርት ዘመኑ ከ100 ሺ ሄክታር በላይ መሬት በሩዝ እየለማ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ ገለጸ።
 
በኦሮሚያ ክልል የግብርናውን ምርትና ማርታማነት ለማሳደግ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ አበራ ወርቁ ገልጸዋል።
 
በ2014/15 የምርት ዘመን በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የሩዝ ሰብል በስፋት ለማልማት ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን ጠቅሰው÷ ከ100 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በሩዝ እየለማ መሆኑን ተናግረዋል።
 
የሩዝ ልማቱ በኢሉባቦር፣ ጅማ፣ ወለጋና ቡኖ በደሌ ዞኖች ላይ እየተከናወነ ሲሆን÷ከታያዘው ዕቅድ በላይ መሬት በሩዝ ሰብል መሸፈኑን አንስተዋል።
 
በክልሉ እስካሁን በስፋት ያልተሰራበት በሻይ ቅጠል ምርት 2 ነጥብ 5 ችግኞች ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ እንደሆነ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
 
በቀጣይ ዓመትም የሻይ ቅጠልን በስፋት በማልማት ወደ ውጭ የመላክ እቅድ እንዳለ ነው የተናገሩት።
 
ከ1 ቢሊን በላይ የቡና ችግኞችን ለማጽደቅ የተከላ ሂደት እየተከናወነ መሆኑንም የቢሮ ሃላፊው ገልጸዋል።
 
የኦሮሚያ ክልል በምርት ዘመኑ በመኸር 205 ሚሊየን ኩንታልና በበልግ 17 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ማቀዱ ታውቋል።
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.