Fana: At a Speed of Life!

አመራሩ ለከተሞች ፈጣን ዕድገት በቅንጅት እንዲሠራ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁሉም የከተማ አመራር ለከተሞች ፈጣን ዕድገት በቁርጠኝነት፣ በታማኝነት እና በተቀናጀ መንገድ ሊሠራ እንደሚገባ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ።
ሚኒስቴሩ ከፌዴራል መንግሥት አመራሮች፣ ከባለድርሻ አካላት፣ ከከተማ ከንቲባዎችና የከተማ አመራሮች ጋር ዛሬ በአዳማ የ2014 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2015 በጀት ዓመት የሴክተር ጉባዔ የዕቅድ ውይይት አካሂዷል፡፡
የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት÷ ዘመናዊና አዳዲስ አሠራሮችን በቴክኖሎጂ በመታገዝ በሁሉም ዘርፎች ደረጃውን በጠበቀ መንገድ ማከናወን ይገባል፡፡
በ2014 ዓ.ም የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ተወዳዳሪ ሆኖ ከፍ እንዲል ለማድረግ የድጋፍና የክትትል ሥራ መከናወኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
እንዲሁም ከሁሉም ከተሞች ጋር በመተባበር በድርቅ፣ በጦርነትና በሰላም እጦት ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ፣ የአረንጓዴ ዐሻራን ተግባራዊ በማድረግ፣ የተለያዩ የቤት ግንባታ አማራጮችን በማቅረብ፣ ከተሞች ገቢያቸውን እንዲያሳድጉ በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.