Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ሱዳን ልዑካን ቡድን የህዳሴ ግድብን ጎበኘ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 9 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ልዩ አማካሪ ኮንግ ቲፕቲፕ ጋትሉዋክ የተመራ ልዑክ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጎበኘ፡፡

ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ኢትዮጵያ የሚገኘው የልዑካን ቡድኑ በዛሬው ዕለት የታላቁ ህዳሴ ግድብን ተዘዋውሮ ተመልክቷል፡፡

በሌላ በኩል ልዑካኑ በብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሥር በሚገኘው የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ አረንጓዴ አሻራ የማኖር መርሐ ግብር ማከናወኑ ተገልጿል፡፡

ልዑካን ቡድኑ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የማሻሻያ ሥራዎችን የጎበኘ ሲሆን÷ በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት በሚኖረው ቆይታም የጸጥታና ደህንነት ተቋማትን ይጎበኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከዚህ ባለፈም ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን በምስራቅ አፍሪካ ሰላምና ፀጥታን በማረጋገጥና ሽብርተኝነትን በመከላከል ረገድ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር የሚያስችሉ ስምምነቶች እንደሚፈጽም ከብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.