በሐረሪ ክልል የቤት ኪራይ ጭማሪን ለመገደብ የወጣው ደንብ ተራዘመ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪና ተከራይ ማስወጣትን ለመገደብ የወጣው ደንብ ለሦስት ወራት ተራዝሟል፡፡
ዜጎችን ከተለያዩ ጫናዎች ለመከላከል ደንቡ ለሦስት ወራት እንዲራዘም የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ወስኗል።
በዚህም ለሚቀጥሉት ሦስት ወራት ተከራዮችን ማስለቀቅና እና የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግ እንደማይቻል ምክር ቤቱ ማሳሰቡን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡
የዜጎችን ጥያቄና አገራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ከዚህ በፊት የመኖሪያ ቤት ተከራዮችን ለማስለቀቅና የቤት ኪራይ ጭማሪ ለመገደብ ደንብ መውጣቱ ይታወሳል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-