የሀገር ውስጥ ዜና

በአዲስ አበባ ከተማ እና የፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ወሰን ማካለል ላይ ውይይት ተካሄደ

By Feven Bishaw

August 16, 2022

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ እና የፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የአስተዳደር ወሰን ማካለልን በተመለከተ በሁለቱ ወገኖች የተደረሰ ስምምነት ላይ የሕዝብ ውይይት ተካሄደ።

ውይይቱ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳን እና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው የተካሄደው።