የሀገር ውስጥ ዜና

በሽረና አክሱም የአፈር ማዳበሪያ እየተሰራጨ ነው

By Alemayehu Geremew

August 16, 2022

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ሽረና አክሱም አካባቢዎች የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮች እየተሰራጨ መሆኑ ተገለፀ፡፡

በሌሎችም የክልሉ አካባቢዎች ያሉ አርሶአደሮችም የዝናቡን ወቅት ተጠቅመው እንዲያርሱና መሬታቸው ጦም እንዳያድር የሚደረገው ድጋፍ መቀጠሉ ተገልጿል፡፡

መንግስት ለትግራይ ህዝብ ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበር አስፈላጊ ድጋፍ እንዲደርስ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡