Fana: At a Speed of Life!

በቦሌ ክ/ከተማ ከ400 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 11 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቦሌ ክፍለ ከተማ በ2014 በጀት ዓመት የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው በዛሬው ዕለት ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኑ።

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ዣንጥራር አባይ ፕሮጀክቶቹን መርቀው በይፋ ስራ አስጀምረዋል።

19 የመማሪያ ክፍሎች እና የአስተዳደር ሕንፃዎች፣ 7 የስፖርት ማዘውተሪያ እና የወጣቶች ስብእና መገንቢያ ማዕከላት፣ አንድ ላቦራቶሪ እና የመድሃኒት አገልግሎት መስጫ ተቋም፣ የቤተ መፃሕፍት ግንባታና እድሳት፣ የ27 ሼዶች ግንባታና እድሳት ሥራዎች ከተገነቡት ውስጥ ይገኙበታል።

የ21 ኪሎ ሜትር የኮብልስቶን መንገድ ሥራ፣ የ28 ኪሎ ሜትር የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦዎችና ካልቨርት ሥራ እንዲሁም አምስት የማኅበረሰብ አቀፍ የፖሊስ ማዕከላት ግንባታ በህብረተሰብ ተሳትፎ መገንባታቸው ታውቋል።

በክፍለ ከተማው ሥር ያሉ ወረዳዎችን ተደራሽ በማድረግም በመንግሥት ወጪና በኅብረተሰቡ ተሳትፎ ከ101 ያላነሱ ፕሮጀክቶች በ403 ሚሊየን ብር ወጪ ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸው ተገልጿል።

በማህሌት ተ/ብርሃን

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.