Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ኮሪያ ሁለት ክሩዝ ሚሳኤል ማስወንጨፏ ተሰማ 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ ሁለት የክሩዝ ሚሳኤሎችን ማስወንጨፏን የደቡብ ኮሪያው የዜና አገልግሎት ዮንሃፕ ዘግቧል፡፡

የደቡብ ኮሪያን ጦር ዋቢ ያደረገው ዮንሃፕ እንደዘገበው ሰሜን ኮሪያ ከሀገሪቱ ምዕራባዊ የባህር ዳርቻ ወደ ቢጫ ባህር ሁለት የክሩዝ ሚሳኤሎችን በዛሬው እለት አስወንጭፋለች፡፡

የሚሳኤል ሙከራው ካለፈው ጥር ወር ወዲህ የመጀመሪያው መሆኑን አር ቲ በዘገባው አስታውሷል።

የአሁኑ ሙከራ ደቡብ ኮሪያ ከአሜሪካ ጋር የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ካደረገች ከቀናት በኋላ የተደረገ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

ፒዮንግያንግ ሁለቱ ሀገራት የሚያደርጉትን ወታደራዊ ልምምድ ጠብ አጫሪ እና በቀጠናው ውጥረትን የሚያነግስ ነው በማለት በተደጋጋሚ ስትኮንን ቆይታለች።

ሰሜን ኮሪያ በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ መሰረት የባለስቲክ ሚሳኤሎችን እንዳታስወንጭፍ የታገደች ሲሆን የክሩዝ ሚሳኤሎችን በተመለከተ ግን ማዕቀብ አልተጣለባትም፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.