Fana: At a Speed of Life!

የሀገርን ገፅታ ከማስጠበቅ አንጻር የተገኙ ልምዶችን ማሳደግ ይገባል ተባለ

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወጪን ከመቆጠብ እና የሀገርን ገፅታ ከማስጠበቅ አኳያ የተገኙ ጥሩ ልምዶችን ማሳደግ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

የአደረጃጀት ለውጥ በተደረገባቸው ሚሲዮኖች ላይ ለሁለት ቀናት ግምገማዊ ውይይት ተካሂዷል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፥ በሁሉም ኤምባሲዎች፣ ሚሲዮኖች እና ቆንስላ ጽህፈት ቤቶች ከወቅታዊ የዲፕሎማሲ ግንኙነት አኳያ በአደረጃጀት፣ በሰው ኃይል ስምሪት እና በአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ተደርጎባቸው ወደ ተግባር መገባቱን አስታውሰዋል፡፡

ወጪን መቆጠብ፣ የሥራ ቦታን ለተገልጋዩ ምቹ ማድረግ እና የሀገርን ገፅታ ማስጠበቅ በሚሉ የሥራ መለኪያዎች የተገኙ ጥሩ ልምዶችን ማሳደግ እንደሚገባም አጽንዖት ሰጥተዋል፡፡

የለውጡ ዋነኛ ግብ የተቋሙን የመፈጸም አቅም በማጎልበት ተደራሽ የሆነ፣ ወጪ ቆጣቢና የሀገርን ጥቅም የሚያስጠብቅ ተቋም መፍጠር መሆኑንም አስታውሰዋል፡፡

አምባሳደሮች በበኩላቸው÷ በተያዘው በጀት ዓመት የተጓደሉ ተግባራትን በማሻሻል እና የላቁ ተግባራትን በማጠናከር የተጀመሩ የለውጥ ሥራዎችን እንፈጽማለን ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

ማሻሻያ እና የአደረጃጀት ክለሳ የተደረገባቸው ሚሲዮኖች እንደ አስፈላጊነቱ ተለይተው የሰው ኃይል ስምሪት እና የበጀት ድልድል እንዲኖራቸው ይደረጋል ተብሏል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.