Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ላለው ሰላምና መረጋጋት ወሳኝ ሀገር ናት-የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጀርመን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን ከጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ፣መካከለኛው ምስራቅ እና ላቲን  አሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል ዶክተር ክርስትያን ባክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

አምባሳደር ሙሉ በኢትዮጵያ  ያለው የጸጥታ ሁኔታ  እየተረጋጋ እና እየተሻሻለ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ሁሉን አቀፍ ብሄራዊ ምክክር ለማድረግ እየተደረገ ያለውን ጥረት ፣ ሦስተኛ ዙር የህዳሴ ግድብ ውሃ ሙሌት  እና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ  ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

አምባሳደሯ በድርቅ ፣ በጎርፍ ፣በግጭት እና በበረሃ አንበጣ ምክንያት ችግር ለደረሰባቸው በአማራ ፣ በአፋር ፣ በትግራይ እና በሶማሌ ክልሎች ለሚገኙ ወገኖች የሰብዓዊ ዕርዳታ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ጠቁመዋል፡፡

በሌላ በኩል  ኢትዮጵያ  ችግር ውስጥ የሚገኙ ሀገራትን ለመርዳት የሰላም አስከባሪ ሃይል በማሰማራት የበኩሏን ሚና እየተጫወተች መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ዶክተር ክርስትያን በበኩላቸው ÷ኢትዮጵያ  በአፍሪካ ቀንድ ላለው ሰላምና መረጋጋት ወሳኝ ሀገር መሆኗን ጀርመን እንደምትገነዘብ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.