Fana: At a Speed of Life!

የቻይና እና ሩሲያ ጦር የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ሊያካሂዱ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና ጦር በሩሲያ በሚካሄደው የቮስቶክ-2022 ስትራቴጂያዊ ወታደራዊ ልምምድ ላይ እንደሚሳተፍ አስታወቀ፡፡

ወታደራዊ ልምምዱ ቤጂንግ ከሞስኮ ጋር ያላትን ስትራቴጂያዊ ትብብር ለማሳደግ እና ለደኅንነት ሥጋቶች ምላሽ ለመሥጠት አቅሟን ለማጠናከር እንደሚያስችላት የቻይና መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በወታደራዊ ልምምዱ ሕንድ፣ ቤላሩስ፣ ታጂኪስታን እና ሞንጎሊያም እንደሚሳተፉ ተመላክቷል፡፡

ልምምዱ ከወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ እና አኅጉራዊ ሁኔታ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም መባሉን ሲጂቲ ኤን ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.