Fana: At a Speed of Life!

የድሬዳዋ ከተማ እና ዩኒቨርሲቲ ከቻይናው ቢንዝሆ ከተማ እና ዩኒቨርሲቲ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ከተማ እና የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከቻይናው ቢንዝዮ ከተማ እና ቢንዝዮ ዩኒቨርሲቲ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡
 
በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ በቻይና ሻንዶንግ ግዛት ቢንዝሆ ከተማ ፍሬያማ የኢትዮጵያ ቀን መከበሩን አስፍረዋል፡፡
 
በመድረኩ በኢትዮጵያ የሚገኙ የኢንቨስትመንት ፣ የንግድ ፣ ባህል እና ቱሪዝም እንዲሁም በሌሎች መስኮች ያሉ አመራጮችን የማስተዋወቅ ስራ መሰራቱን ተናግረዋል፡፡
 
በመርሐ ግብሩ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አመራሮች እንዲሁም የድሬዳዋ ከንቲባ በበይነ መረብ መሳተፋቸውን ጠቁመዋል፡፡
 
በዕለቱም የድሬዳዋ ከተማ እና የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከቻይናው ቢንዝሁ ከተማ እና ቢንዝሁ ዩኒቨርሲቲ ጋር ትብብራቸውን ማጠናከር የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸውን ነው የገለጹት፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.