የሀገር ውስጥ ዜና

የፌዴሬሽን ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ እየመከሩ ነው

By Melaku Gedif

August 17, 2022

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች ነሐሴ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ከአስቸኳይ ጉባኤው አጀንዳዎች ጋር ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው፡፡

በስብሰባው የማንነት፣ የአስተዳደር ወሰንና የሰላም ግንባታ፣ የመንግሥታት ግንኙነት፣ የዴሞክራሲያዊ አንድነትና የሕገ መንግሥት አስተምህሮ፣ የድጎማና የጋራ ገቢዎች ድልድል ጉዳይ እና የሕገ መንግሥት ትርጉምና ውሳኔ አፈጻጸም ክትትል ቋሚ ኮሚቴዎች ናቸው እየተሳተፉ የሚገኙት፡፡

ቋሚ ኮሚቴዎቹ በአጀንዳዎቹ ላይ በመምከር ለምክር ቤቱ የውሳኔ ሃሳቦችን ያቀርባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡