Fana: At a Speed of Life!

እስራዔል እና ቱርክ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማደስ ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራዔል እና ቱርክ ያቋረጡትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ነበረበት ለመመለስ መሥማማታቸው ተገለጸ፡፡

የእስራዔል ጠቅላይ ሚኒስትር ያይር ላፒድ የየሀገራቱ አምባሳደሮች እና ቆንስላ ጀነራሎች ወደ ቀድሞ መደበኛ ሥራቸው ይመለሳሉ ሲሉ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶኻን ጋር መወያየታቸውንም ገልጸዋል፡፡

የሀገራቱን ግንኙነት ማሳደግ የህዝብ ለህዝብ ትሥሥሩን ለማጠናከር እንደሚረዳ አስታውቀዋል።

ከዚህ ባለፈም የሀገራቱን የኢኮኖሚ፣ የንግድ፣ የባሕል ግንኙነት ለማሳደግ እና ቀጠናዊ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን እንደሚረዳም አመላክተዋል።

የሀገራቱ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ነበረበት መመለስ ለቀጠናው መረጋጋት አወንታዊ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ማለታቸውንም ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል።

በፈረንጆቹ 2010 ላይ ከቱርክ የተነሱ ጀልባዎች እስራኤል በጋዛ ሰርጥ የጣለችውን እገዳ ጥሰው ለማለፍ መሞከራቸውን ተከትሎ በተፈጠረ አለመግባበት የሀገራቱ ግንኙነት መቋረጡ ይታወሳል።

በወቅቱ ም ከእስራኤል ጦር ጋር በተፈጠረ አለመግባባት 10 ቱርካውያን ለህልፈት መዳረጋቸውም የሚታወስ ነው።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.