የሀገር ውስጥ ዜና

1 ሺህ 25 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Alemayehu Geremew

August 17, 2022

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 11 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው እለት በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ስራ 1 ሺህ 25 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስመመለሳቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከተመላሾቹ ውስጥ 880 ወንዶች፣ 129 ሴቶች እና 16 ህፃናትና እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ ተደርጓል፡፡

እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ቁጥራቸው 66 ሺህ 561 ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።