አምባሳደር ስለሺ ከኢትዮ-አሜሪካ ንግድ ምክር ቤት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ስለሺ በቀለ ከኢትዮ-አሜሪካ የንግድ ዘርፍ ማህበር የቦርድ አባላት ጋር በአገራዊና የቢዝነስ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
አምባሳደር ስለሺ በውይይቱ ላይ በኢትዮጵያ ተግባራዊ እየተደረገ ስላለው የሪፎርም ሥራ አብራርተዋል፡፡
ኢትዮጵያ በአጎዋ የገበያ እድል እንደገና ተጠቃሚ እንድትሆን እየተሠሩ ያሉ ሥራዎችን አስረድተዋል፡፡
በቀጣይ የንግድ ም/ቤቱ የኢትዮጵያ ኩባንያዎችን ከአሜሪካ ድርጅቶች ጋር የማስተሳሰር ሥራ እንዲሠራ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
እንዲሁም በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ንግድና ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ በጋራ ለመሥራት መግባባት ላይ መደረሱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!