Fana: At a Speed of Life!

የፌዴሬሽን ም/ቤት በደቡብ ክልል ስር የነበሩ 6 ዞኖችና 5 ልዩ ወረዳዎች ያቀረቡትን የውሳኔ ሀሳብ ተቀብሎ ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ወሰነ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ስር የነበሩ 6 ዞኖችና 5 ልዩ ወረዳዎች በአንድ ክልል እንዲደራጁ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ተቀብሎ ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ውሳኔ አሳለፈ።
 
ውሳኔውን በ5 ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ ነው ያጸደቀው።
 
በአንድ ክልል ሆነው እንዲደራጁ የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጌዴኦ እና ኮንሶ ዞኖች እንዲሁም የደራሼ፣ አማሮ፣ ቡርጂ፣ አሌ እና ባስኬቶ ልዩ ወረዳዎች ናቸው።
 
ምርጫ ቦርድ ህዝበ ውሳኔውን እንዲያካሂድና ውጤቱንም ለምክር ቤቱ እንዲያሳውቅ አቅጣጫ አስቀምጧል።
 
ቀሪዎቹ የሀድያ ዞን፣ ሀላባ ዞን፣ ከንባታ ጠንባሮ ዞን፣ ጉራጌ ዞን፣ ስልጤ ዞን እና የም ልዩ ወረዳ በነባሩ ክልል ይቀጥላሉ ተብሏል።
 
በኃይለኢየሱስ ስዩም
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.