Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ30 ሚሊየን ብር የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገለት

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በኢሺ ፕሮግራም በጋምቤላ ከተማ ለሚገኘው ኦፔኖ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 30 ሚሊየን ብር የሚገመት ለአይሲቲ መሠረተ ልማት የሚሆኑ የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርጓል።

የኮሌጁ አስተዳደር ምክትል ዲን አቶ ጊል ማንጎግ እንዳሉት÷ የተደረገው ድጋፍ የኮሌጁን የቴክኖሎጂ ሽግግር አቅም በማሳደግና ወጭ በመቀነስ የሥልጠና ጥራትን ለማስጠበቅና የአገልግሎት አሠጣጥን ለማዘመን ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ።

ድጋፉ ጄኔሬተር እና ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተርን ጨምሮ በርካታ የአይሲቲ ቁሳቁሶች እንደሚገኙበት ተናግረዋል።

የክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡቦንግ ኡጉታ ÷ ኮሌጁ የቁሳቁስ ዝርጋታውን በቶሎ እንዲያጠናቅቅ እና ወደ ትግበራ እንዲገባ በትኩረት መስራት እንደሚኖርበት አስታውቀዋል።

የኢሺ ፕሮጀክት ማናጀር ዶክተር ክንዳለም ዳምጤ በበኩላቸው÷ ድጋፉ በሃገር ደረጃ በተመረጡ 20 ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች የአይሲቲ መሠረተ ልማት የማስጀመር እቅድ አካል መሆኑን መናገራቸውን ከጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.