የሀገር ውስጥ ዜና

የቆቃ ኃይል ማመንጫ ሲደረግለት የነበረው ጥገና ተጠናቀቀ

By Shambel Mihret

August 18, 2022

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ20 ሚሊየን ብር ወጪ ከቆቃ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ግድብ የሚወጣውን ውሃ ፍጥነትና እንቅስቃሴ ለመቀነስ የሚያገለግለው “የስቲሊንግ ቤዚን” የጥገና ስራ ተጠናቀቀ፡፡

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ግንባታ የራስ ኃይል የሲቪል ሥራዎች ጥገና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ግርማ መንገሻ እንዳስታወቁት በውሃ ማስተንፈሻዎች በኩል ከግድቡ የሚወጣው ውሃ የሚያርፍበት መሬት እየተሸረሸረ በመምጣቱ የሰቲሊንግ ቤዚን ጥገና ስራ መከናወኑን ተናግረዋል፡፡

በ20 ሚሊየን ብር ወጪ የተከናወነው የጥገና ሥራ የቀድሞውን የአርማታ ወለል በማፍረስና በቦታው የነበረውን ተፈጥሯዊ ዐለት በማስወገድ በግድቡ ግርጌ ባለው የመሬት ወለል ላይ በብረት ንጣፍ የተከናወነው የአርማታ ሙሌት ሥራ የግድቡ መሰረት በውሃ እንዳይሸረሸር የሚያደርገው ነው፡፡

ይህም የግድቡን ደህነነት ለመጠበቅ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው መሆኑንና ጣቢያውን ለተጨማሪ ዓመታት አገልገሎት እንዲሰጥ የሚያስችለው መሆኑን ሥራ አስኪያጁ መግለፃቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ላለፉት 62 ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው የቆቃ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ 43 ሜጋ ዋት የማንጨት አቅም ያለው መሆኑ ይታወቃል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!