Fana: At a Speed of Life!

በአውሮፓ የተከሰተው ድርቅ የባህር ትራንስፖርት አገልግሎትን ማስተጓጎሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)  በአውሮፓ የተከሰተው ድርቅ የባህር ትራንስፖርት አገልግሎትን እያስተጓጎለ መሆኑን የተለያዩ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡

በአህጉረ አውሮፓ እየተከሰተ ባለው ድርቅ ምክንያት የሐይቆች እና የወንዞች ውሃ መጠን እየቀነሰ በመምጣቱ የባህር ትራንስፖርት አግልግሎት ችግር ውስት መግባቱ ተገልጿል፡፡

በዚህም ምክንያት እንደ ጀርመን ያሉ አንዳንድ ሀገራት  ለኃይል ምርቶቻቸው አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶች እና መሳሪያዎችን  ከባህር ትራንስፖርት ይልቅ ለባቡር ትራንስፖርት ቅድሚያ መስጠታቸው ነው የተዘገበው፡፡

በተጨማሪም ድርቁ በሰርቢያም የተከሰተ ሲሆን፥  በሀገሪቱ በሚገኘው በኖቪሳድ ሐይቅ የሚንቀሳቀሱ ጀልባዎች በውሃው መቀነስ ሳቢያ እንቅስቃሴያቸው ተገቶ ባሉበት ቆመው መታየታቸውም ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም በፈረንሳይ የሚገኙት የዳንዩብ እና ሎየር ሐይቆች መጠናቸው በመቆነሱ የጀልባዎች እንቅስቃሴ ከመቆሙ በተጨማሪ በሐይቆች አካባቢ የሚገኙ ዳርቻዎች ደርቀው መታየታቸውንም ሲጀቲኤን ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.