Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ከ845 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከ 845 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ ፕሮጀክቶችን መረቁ፡፡
ከንቲባዋ በመጀመሪያ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 የሚገኘውን የምገባና የህይወት ክህሎት ስልጠና ማዕከል መርቀዋል፡፡
ቢ ኬ ጂ ፋውንዴሽን ያስገነባው ማዕከሉ፥ 500 ዜጎችን በቀን ሁለት ጊዜ መመገብ የሚያስችል ነው።
በአጠቃላይ እንደ ክፍለ ከተማ ዛሬ የተመረቁ ሶስት ተመሳሳይ የምገባ ማዕከላት በቀን 2 ሺህ አቅመ ደካሞችን እንደሚመግቡ ተጠቁሟል፡፡
የምገባ ማዕከሉ በኢትዮ ገልፍ ተራድኦ ድርጅት የተገነባ መሆኑንም ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በተጨማሪም ከንቲባ አዳነች ጋዜቦ ወይም ዋሽንግተን ዲሲ አደባባይን የመረቁ ሲሆን÷ አደባባዩ በርካታ ኢትዮጵያውያን የሚኖሩባት ዋሽንግተ ከተማን እንዲወክል ቋሚ ሃውልት የተሰራለት መሆኑ ተገልጿል፡፡
በአጠቃላይ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በዛሬው ዕለት ከ845 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ 105 ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች መመረቃቸው ተመላክቷል፡፡
እነዚህ ፕሮጀክቶች 250 ሺህ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሲሆን÷ ለ5 ሺህ 983 ሰዎችም የስራ ዕድል ይፈጥራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.