Fana: At a Speed of Life!

ፖሊስ ሀገር አቀፍ የፀጥታ ውይይት እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፌደራል ፖሊስ ሀገር አቀፍ የፀጥታ ውይይት እያካሄደ መሆኑ ተገለጸ፡፡
በውይይቱ ላይ የሁሉም ክልሎችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ኮሚሽነሮች፣ ኮሚሽነር ጀነራሎች እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል::
ኮሚሽነር ደመላሽ ገ/ሚካኤል በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ውይይቱ የሀገርን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የጋራ መግባባትና አተገባበር እንዲኖር ያግዛል ብለዋል::
በ2015 ዓ.ም በሚኖሩ ሕዝባዊና ሃይማኖታዊ በዓሎች በሰላም እንዲከበሩ የተቀናጀ ሥራ መሥራት ይኖርብናል ብለዋል::
የሀገርን ሰላም ለማደፍረስ በተለያዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ሽብርተኞችን ሴራ ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በመቀናጀት ማክሽፍ ይኖርብናል ነው ያሉት፡፡
ሁሉም የውይይቱ ተሳታፊዎች ከውይይቱ የሚገኘውን ግብአት በየአካባቢያቸው ወደ ተግባር ለመቀየር አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡
በቀጣዮቹ 3 ወራት ውስጥ የሚተገበሩ እቅዶች ላይም ውይይት ይካሄዳል ተብሏል::
በዘቢብ ተክላይ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.