የሀገር ውስጥ ዜና

የቡሄ በዓል ሃይማኖታዊና ባህላዊ  ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ በታቦር ተራራ እየተከበረ ነው

By Mikias Ayele

August 19, 2022

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቡሄ በዓል በደብረ ታቦር ከተማ ሃይማኖታዊና ባህላዊ  ስርዓቱን  በጠበቀ መልኩ በድምቀት እየተከበረ ነው።

እንደ ሀይማኖት አባቶች ገለፃ የደብረታቦር በዓል የብርሃን እና የመገለጥ በዓል ሲሆን፥ እየሱስ ክርስቶስ  በታቦር ተራራ ተገልጦ ብርሃን የታየበትን ቀን ነው ፡፡

ይሄው የመገለጥ እና  የብርሃን በዓል የሆነው ቡሄ  በተለይም የበዓሉን ስም በያዘቺው በጎንደሯ ደብረታቦር ከተማ ወግና ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ በርካታ እንግዶች በተገኙበት እየተከበረ ይገኛል።

በበዓሉ  አከባበር የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበልን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናት እና እንዲሁም ግጥሪ  የተደረገላቸው አርቲስቶች፣ ምሁራን እና ሌሎቹም ታድመዋል።

 

በታሪኩ ለገሰ