Fana: At a Speed of Life!

ምዕራባውያን ለዩክሬን የሚያደርጉት ወታደራዊ ድጋፍ እየደረቀ መምጣቱን ጥናት አመላከተ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ኅብረት አባል ሀገራት ለዩክሬን አዲስ ወታደራዊ ድጋፍ ለማድረግ ቃል አለመግባታቸው ተነገረ፡፡

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የተደረገ ጥናት በየካቲት ወር መጨረሻ ላይ ሩሲያ ወታደሮቿን ወደ ዩክሬን ከላከች በኋላ የአውሮፓ ኅብረት አባል ሀገራት ወታደራዊ ዕርዳታ ለዩክሬን ለመላክ ቃል መግባት ካቆሙ 20 ቀናት መቆጠራቸውን አመላክቷል፡፡

በጉዳዩ ላይ መረጃ ይፋ ያደረገው በዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ላይ ጥናቶችን በመሥራት የሚታወቅ ጀርመን የሚገኝ ኪየል የተሰኘ ኢኒስቲትዩት ነው፡፡

እንደ ጥናቱ የኅብረቱ አባል ሀገራት ለዩክሬን የሚሰጡትን ወታደራዊ ዕርዳታ እየቀነሱ መምጣታቸውን የሚያሳይ ምልክት እየታየ ነው።

ኢኒስቲትዩቱ ለቭላድሚር ዜሌንስኪ የቀረበውን ዓለም አቀፋዊ ወታደራዊ አቅርቦት ፣ የገንዘብ እርዳታና ሰብአዊ ድጋፍ ሲከታተል እና በዝርዝር ሲለካ ቆይቷልም ነው የተባለው፡፡

የጥናቱ መረጃ እንደሚያሳየው ከአውሮፓ ለዩክሬን የሚደርሰው ወታደራዊ ዕርዳታ ከሚያዝያ ወር መጨረሻ ጀምሮ በሚታይ መልኩ እየቀነሰ መምጣቱን ፋርስ ኒውስ እና ፖለቲኮ ዘግበዋል፡፡

አንድ የአሜሪካ የመረጃ ምንጭ በበኩሉ ከብሪታኒያ ፣ፖላንድ እና አሜሪካ ለዩክሬን የሚላከውን ወታደራዊ ዕርዳታ ባለማድረስ ጀርመንን እና ፈረንሳይን ተጠያቂ ማድረጉም ተነግሯል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.